
አዲስ መጽሐፍ

አንጋፋው ደራሲ ፍቅረማርቆስ ደስታ የሐመር ሕዝብ ባህል ላይ ባተኮሩት እጅግ ተወዳጅ በሆኑት ተከታታይ ‘ኤትኖግራፊክ’ ልብወለድ ድርሰቶቹ ይታወቃል። አሁን ደግሞ “የሚሳም ተራራ” የተሰኘ ድንቅ መጽሐፉን ለበርካታ ዓመታት በጉጉት ሲጠብቁ ለነበሩት አንባቢዎቹ ይዞ ቀርቧል። በዚህም የግለታሪክ መጽሐፉ ፍቅረማርቆስ የሕይወት ጉዞውን ትዕይንታዊ በሆነ ውብ ቋንቋ በመተረክ የትዝታ ብልጭታዎቹን (ከኢትዮጵያ እስከ አሜሪካ፣ ከልጅነት እስከ ጐልማሳነት) ሳይሰስት ያጋራል።
ፍቅረማርቆስ በአንባቢዎች እስከዛሬ ከፍተኛ አድናቆትን ያስገኘለትን ከቡስካ በስተጀርባ የተሰኘውን የበኩር ድርሰቱን በ1987 መጀመሪያ ለንባብ አብቅቷል። ከዛም በተከታታይ ተወዳጅ ልብወለድ ድርሰቶቹን – “ኢቫንጋዲ” (1990 ዓ.ም) እና “የዘርሲዎች ፍቅር” (1991 ዓ.ም) አሳተመ። መጽሐፎቹም በርካታ የአገር አቀፍ ሽልማቶች አሸናፊ ሆነዋል።
በሚቀጥሉት አመታትም አትኩሮቱን ከደቡብ ኦሞ በማዞር “አቻሜ” (1992 ዓ.ም) እና “የንሥር ዐይን” (1993 ዓ.ም) የተሰኙ ታሪካዊ ልቦለዶቹን ለአንባቢዎቹ አቀረበ። “Land of the Yellow Bull” (1995 ዓ.ም) የተሰኘ የእንግሊዘኛ ልብወለድም አሳትሟል። ከዚህ ባሻገርም “ጃገማ ኬሎ – የበጋው መብረቅ” (2001 ዓ.ም) በሚል ርእስ የጀግናው አርበኛን የሕይወት ታሪክ በተለመደው ውብ ትረካው አስነብቦናል። በደቡብ ኦሞ ላይ በሚያተኩሩ ዶኩሜንተሪ ፊልሞች – “Becoming a Man in Africa” (2005) እና “Black Samurai” (2006) ላይም ተሳትፏል።
Dr. Alula Pankhurst“Fikremarkos’s works have helped in popularizing the aims and role of social anthropology and contribute towards furthering cultural understanding, exchange and coexistence”
አዲስ መጽሐፍ
$ 25.00
ትናንታችን ውስጥ ያለፍነው ዛሬ አለ፤ ነጋችን ውስጥም ዛሬ ሕያው ሆኖ ይኖራል። በሕይወት ዑደት ሽቅብ ቁልቁል እንወጣለን፣ እንወርዳለን፣ እናጣለን፣ እንቀበላለን . . . ፀሐይ ትገባለች፣ ትወጣለች – ሰዓቷን ጠብቃ በዛቢያዋ ላይ እየተሽከረከረች!ትናንታችን ዝምታም ነው – አጠንክሮን፣ አስተምሮን የሚያልፍ፤ ዘወር ብለን ስናየው በዐይናችን የምንስመው . . . የምንዘክረው!
የሚሳም ተራራ
“… ባልተወሳሰበ አገላለጽ የተተረከ ብሩህነት ያለው፣ የገጸባሕርያቱ ድርጊትና ማንነት የሚታይበት፣ ታሪኩን እስከ ማብቂያው እንድንከታተል የሚያደርጉ አጋጣሚዎችና ሁነቶች ያሉበት ልብ ሰቃይ ድርሰት ነው”
ፕሮፌሰር ዘሪሁን አስፋው




Leave a reply to Zelalem Getachew Cancel reply